መካከለኛ ምስራቅ
የሳውዲ አረቢያ ልዑል ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አል ቡርሃን ጋር በሪያድ መወያየታቸው ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/04/2018፡- የዘውዱ ልዑል እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን ሳልማን ትላንት ሪያድ በሚገኘው አል-ያማማህ ቤተ መንግሥት ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና አብረዋቸው ከሄዱት ልዑካን ቡድን ጋር ተገናኝተዋል።
በስብሰባው ወቅት በሱዳን ውስጥ የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን፣ አንድምታዎቻቸውን እና በአገሪቱ ውስጥ ደህንነት እና መረጋጋትን ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶችን መገምገማቸው ተገልፀዋል።
በስብሰባው ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ልዑል ካሊድ ቢን ሳልማን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የካቢኔ አባል እና የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ዶ/ር ሙሳድ አል-አይባን፤ የፋይናንስ ሚኒስትር መሐመድ አል-ጃዳን እና የሳዑዲ አምባሳደር አሊ ጃፋር ተገኝተዋል።
በጄኔራል አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ኃይል ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ጋር ጦርነት ጦርነት ላይ ሲሆን ታጣቂ ብድኑ ሁሉንም የዳርፉርን እና የኮርዶፋንን ክፍሎች ሲቆጣጠር፣ የጦር ኃይሉ ደግሞ ዋና ከተማዋን ካርቱምን እና የምስራቃዊ፣ የመካከለኛው እና የሰሜን የአገሪቱን ክልሎች ተቆጣጥሮ ይገኛል።



