አፍሪካ

የተባበሩት መንግስታት የአቢዬ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በቅርቡ ከደረሰው ገዳይ ጥቃት በኋላ የመከላከያ እርምጃዎችን አጠናክሪያለሁ ኣለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/04/2018፡- ‘የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ሃይል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ሮበርት ያ አፍራም ሁኔታውን ለመገምገም እና ከሰላም አስከባሪ አባላት እና ሌሎች ተዛማጅ አካላት ጋር ለመነጋገር ካዱግሊን መጎብኘታቸው ታውቀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል (UNISFA) በደቡብ ኮርዶፋን ካዱግሊ በሚገኘው የሎጂስቲክስ ጣቢያ ላይ የድሮን ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ “ሰራተኞቹን እና ተቋማቱን ለመጠበቅ ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች ወስዷል” ብሏል።

የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሉ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ስድስት የባንግላዲሽ የሰላም አስከባሪዎችን ገድሎ ዘጠኝ ሌሎችን ማቁሰሉን ይታወቃል።

“ተልእክውን ሰራተኞቹን እና ተቋማቱን ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ወስዷል፣ ይህም የሰራተኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ በካዱጊሊ የሎጂስቲክስ ጣቢያ የመከላከያ እርምጃዎችን በማጠናከር እና ሁኔታውን ለመገምገም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ ነው” ብሏል ጄነራሉ።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት የጦር ወንጀሎችን ሊያካትቱ እንደሚችሉ እና ወንጀለኞቹ ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሰጡትን መልእክት አመልክተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates