ፖለቲካ

ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የዕውቅና ሠርተፍኬት መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/04/2018፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም የሚያካሂደውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ 45 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የዕውቅና ሠርተፍኬት ሰጥቻለሁ አለ።

ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ፤ የዕውቅና ሠርተፍኬቱን “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011″ እንዲሁም በ”የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች ፈቃድ አሰጣጥ፣ አሠራር እና ሥነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 5/2012” መሠረት በተሰጠው ሥልጣን መስጠቱን ገልጿል።

በዚህም የቦርዱን መስፈርት አሟልተው የተመረጡት 45 ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መጪውን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመታዘብ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች፤ የታዛቢዎችን የምዝገባ ሂደት ቀልጣፋ መረጃ አደረጃጀቱንም ዘመናዊ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀው “የበይነ-መረብ ላይ ምዝገባና መረጃ አደረጃጀትን” አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ከጥቅምት 25 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. መስጠቱን አስታውሷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates