የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ በሱዳኑ ፈታን ድጋፍ ሓይል ጥቃት የተገደሉበት አባላቱን ሸኘ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡- የተባበሩት መንግስታት የአቢዬ ጊዜያዊ የጸጥታ ኃይል እሁድ እለት በደቡብ ኮርዶፋን ግዛት ዋና ከተማ በካዱግሊ በሚገኘው ተቋማቱ ላይ የድሮን ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የሞቱና የቆሰሉ የሰላም አስከባሪዎችን ወደ አቢዬ ክልል አስወጥቷል።
ሶስት ድሮኖች ቅዳሜ ዕለት የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ካምፕ ላይ ኢላማ አድርገዋል የሚሉት መረጃዎች፣ በዚህ ስድስት የባንግላዲሽ የሰላም አስከባሪዎችን ገድለዋል፤ ሌሎች ስምንት ደግሞ ቆስለዋል።
የሱዳን መንግስት ክስተቱን በማውገዝ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎችን ጥፋተኛ ያደረገ ሲሆን፣ የባንግላዲሽ ጦር ደግሞ ጥቃቱን “በተገነጠሉ የታጠቁ ቡድኖች” የተፈፀመ መሆኑን ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለጥቃቱ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን የጠየቁ ሲሆን ነገር ግን ጥፋቱን ለአንድ የተወሰነ ወገን አልሰጡም።
የወታደራዊ ምንጮች ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ከጋና የመጡ የሕክምና ባለሙያዎችን የያዘ የድርጅቱ አውሮፕላን ስድስቱን አስከሬኖች እና ሰባት የቆሰሉትን ሰዎች ለማውጣት ካዱግሊ አረፍዋል።
የባንግላዲሽ ጦር በሎጅስቲክስ ጣቢያው ላይ የደረሰውን ጉዳት ያረጋገጠ ሲሆን አንድ ወታደር ቀዶ ጥገና ተደርጎለት በቅርበት ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ዘግቧል፣ ሌሎች ሰባት ደግሞ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ወደሚገኙ የላቀ የሕክምና ተቋማት በአየር ተወስደዋል ተብለዋል።
ባንግላዲሽ “ጭካኔ የተሞላበት የሽብር ጥቃት”ን በማለት አውግዘዋለች፤ የሰላም አስከባሪዎቿ መስዋዕትነት አገሪቱ ለዓለም አቀፍ ሰላም ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አረጋግጣለች።
ይህ በሱዳን ጦር እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሓይሉ መካከል በሚያዝያ 2015 ዓ/ም ጦርነት ከተነሳ ወዲህ በአቢዬ ግዛት ውስጥ በሚንቀሳቀሰው የተባበሩት መንግስታት ተልዕኮ ላይ በዓይነቱ የመጀመሪያው ጥቃት እንደሆነም ተገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ የሱዳን ህዝብ ትላንት በተለያዩ የሱዳን ዋና ዋና ከተሞች የጦር ኃይሉን ለመደገፍ ሰልፎች አድርገዋል፡፡
ትላንት በደርዘን በሚቆጠሩ የሱዳን ከተሞችና ህዝባዊ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆኑ፤ ዓላማውም ለሰራዊቱ ድጋፍ ለማሳየት እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚደገፈውን እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ላለው የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ተቃውሞ ለማሰማት ነው፡፡



