ዲፕሎማሲ

‹‹ኢትዮጵያ ከሙስሊሙ አለም ጋር የባህል ትስስር ያላት ናት›› ሲሉ የኢራን አፈጉባኤ ተናገሩ፡፡

የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ መሀመድ ጋሊባፍ ለኢትዮጵያው አቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/04/2018፡-  አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለ2 ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ቴሄራን ያቀኑን የኢራን አፈጉባኤ ያቀረቡላቸውን ግብዣ ተከትሎ መሆኑን ተገልፀዋል፡፡

የኢራኑ አፈጉባኤ ባለፈው አመት በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

አፈጉባኤ ጋሊባፍ በአፍሪካ ከፍተኛ ህዝብ ካላቸው አገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ሙስሊም ህዝብ ያላት ከመሆኗም በላይ ከሙስሊሙ አለም ጋር የባህል ትስስር ያላት ናት›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በኢትዮጵያና በኢራን መካከል ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከተፈጠረም 70 አመታት እንዳለፉትም ጠቅሰዋል፡፡

ይህንን ትስስር በሁለትዮሽ ስምምነት ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀውም የጉብኝቱ አላማ ኢራን በአፍሪካ ቀንድ አገራት ውስጥ በባህል፣ ኢኮኖሚና ፖለቲካ ያላትን ተደራሽነት ካላት አላማ ጋር የተገናኘ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋት የባህር መስመሮችን በስትራቴጂ መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

ጨምረውም በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ለመመስረት እየሰራ ያለው ኮሚቴ በቅርቡ ስድስተኛውን ስብሰባውን እንደሚያከናውን ገልፀው የኮሚሽኑ መመስረት ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ማስረዳታቸውን የኢራን መህር የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates