አፍሪካ

ኤርትራ ከኢጋድ አባልነቷ በድጋሚ መውጣቷን አስታወቀች

"የቀጠናውን ፍላጎት ማሳካት ተስኖታል" ስትል ለመውጣቷ በምክንያትነት አቅርባለች

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/04/2018፡- ኤርትራ ቀጣናዊ ህብረት ከሆነው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) መውጣቷን የሀገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በይፋ አሳወቀ።

አስመራ ለኢጋድ ዋና ጸሐፊ በላከችው መልእክት፤ ለውሳኔው መነሻ የሆነው “ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ድክመት በማሳየቱ” እና በቀጣናው ጉዳዮች ላይ በሚጫወተው “ጎጂ ሚና” መሆኑን ገልጻለች።

ኤርትራ እ.ኤ.አ. በ1993 ኢጋድ እንደገና ሲዋቀር፣ ለቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ለኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር እንደ ዋና መሣሪያ ሆኖ የሚያገለግል ተቋምን ለመገንባት ከሌሎች አባል ሀገራት ጋር በመስራት ወሳኝ ሚና እንደተጫወተች አስታውሳለች።

ይሁን እንጂ መግለጫው፣ በሂደት እና በተለይም ከ2005 ጀምሮ (እ.ኤ.አ)፣ ኢጋድ የቀጣናውን ህዝቦች ተስፋና ፍላጎት ከማሳካት ይልቅ፣ በተወሰኑ አባል ሀገራትና በተለይም በኤርትራ ላይ እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ በመሆን ጎጂ ሚና ተጫውቷል ብሏል። በእነዚህም ድርጊቶች ምክንያት አስመራ በጎርጎሮሳውያኑ ሚያዚያ ወር 2007 ከአባልነቷ ለመውጣት መገደዷን መግለጫው አክሎ አብራርቷል።

ኤርትራ ኢጋድ ለሪፎርም ያቀረበችውን ጥሪ ሰምቶ ያለፈውን ታሪኩን ያስተካክላል በሚል ተስፋ፣ በጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 2023 አባልነቷን እንደገና አጠናክራለች። ሆኖም፣ የሀገሪቱ መንግሥት ተቋሙ “ሕጋዊ ግዴታዎቹን መካድ ቀጥሏል” ያለ ሲሆን፤ ይህም “ጠቀሜታውንና ሕጋዊ ሥልጣኑን እያዳከመው መጥቷል” ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates