ማህበራዊ
በአውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ተደረገ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 203/04/2018፡- ሀገሪቱ እንደ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ እና ሬዲት ባሉ መድረኮች ላይ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች እንዳይኖራቸው የሚከለክል ህግ ተግባራዊ አድርጋለች።
የማህበራዊ ሚድያ ኩባንያዎች ይህንን አዲስ ህግ ካላከበሩ እስከ 49.5 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡
የሃገሪቱ መንግስት እገዳው ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚደርሱ ስጋቶችን ለመቀነስ ያለመ ነው።
ህጉ ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከ16 ዓመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች በቀጥታ እንዲወጡ/እንዲወገዱ የተደረገ ሲሆን ይህ እርምጃ የወሰዱት ማህበራዊ ሚድያዎች ቲክቶክ፣ ዩትዩብ፣ ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ፣ ስናፕቻት፣ ሬዲት፣ ኤክስ፣ ትዊች፣ ኪክ፣- ትሬድስ ናቸው።
ዋትስአፕ ፣ ሜሴንጀር፣ የኢሜል አገልግሎቶች ፣ የኦንላይን ላይ ጨዋታዎች እና የተለያዩ ትምህርታዊ መሳሪያዎች ከእገዳው ነፃ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ እና ማሌዥያን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት መንግስታት የአውስትራሊያን አካሄድ ለመተግበር እያጤኑ እንደሆኑም መረጃው ጠቅሷል።
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማህበራዊ እንዳይጠቀሙ በህግ የከለከለች ቀዳሚ ሀገራ ሆናለች።



