የተለያዩ

የ2018ቱ የጂ ፓወር ቲክቶክ ኮንቴንት ክሪኤቲቭ አዋርድ አሸናፊው አዶናይ ብርሃነ በፖሊስ መያዙ ታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/04/2018፡- የፌደራል ፖሊስ ትላንት ማምሻው ባወጣው መረጃ መሰረት ቲክቶኮር አዶናይ ብርሃነ ከጓደኛው ጃኒ ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።”

አዶናይ ብርሃነ ሀ/ሚካኤል በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው ‎ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር በዋሉበት የወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው ” ሲል ፖሊስ አስታውቋል።

“ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን እየተጠቀሙ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመልካም ሥነ ምግባር ተቀርጾ ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራትን እንዳያከናውንና በተቃራኒው በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህል ለመጫን የሚደረገው ተግባር ለመከላከል የጀመርኩትን ምርመራ አጠናክሬ እቀጥላለሁ ” ሲልም ፖሊስ አስታውቋል።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቲክቶኮሮች ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣ በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣ መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣ ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርያም ‎በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates