በ2025 ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች መገደላቸው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ከአምስት መቶ በላይ ደግሞ በእስር እንደሚገኙ ፌደሬሽኑ ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/04/2018፡- የዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) ፕሬዝዳንት ዶሚኒክ ፕራዳሊ ሰባት ሴቶችን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ 111 ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች እንደተገደሉ ተናግረዋል። ከእነዚህ ውስጥ ዘጠኙ ከአፍሪካ ናቸው ብሏል።
በየዓመቱ 91 ጋዜጠኞች ይሞታሉ፣ ፌዴሬሽኑም መረጃ መሰብሰብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የ3,156 ጋዜጠኞችን ሞት መዝግቧል ብለዋል።
በጋዛ በ2025 የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 69 መድረሱን ያመለከተው ሪፖርቱ በ2025 በወጣ ሪፖርት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ 111 ጋዜጠኞች እንደተገደሉ ተረጋግጧል፡፡
ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን በ2025 ባወጣው ሪፖርት 111 ጋዜጠኞች እንደተገደሉ ሲጠቅስ አምስት መቶ ያህሉ በእስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡
ሕይወታቸው ካለፈ ጋዜጠኞች መካከል ስልሳ ዘጠኙ በጋዛ የተገደሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በሩሲያ ዩክሬን ጦርነትም አስር ጋዜጠኞች ሕይወታቸው አልፏል ብሏል ሪፖርቱ፡፡
ሪፖርቱ በ2025 የጋዜጠኞች ሞት እንደጨመረ ገልጾ ዓለም ዓቀፍ ሕግ መጣሱ እና የፕሬስ ነጻነት እየተከበረ አለመሆኑን አያይዞ ጠቅሷል፡፡
በአህጉረ አፍሪካ በተለይም በሱዳን ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት የተነሳ ጋዜጠኞች ጥቃት እንደሚደርስባቸውም ያመለከተው ዘገባው ሞዛምቢክ፣ ሶማሊያ እና ዚምባብዌም ጋዜጠኞች የተገደሉባቸው ሀገራት መሆናቸው ነው የተዘገበው ፡፡



