የተለያዩ

ቲክቶኮሮቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/03/2018- “ከሀገራችን ባህልና ሥነ-ምግባር ያፈነገጠ አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ ተጠርጣሪዎች ላይ  ምርመራ ጀምሬያለሁ ” አለ የፌዴራል ፖሊስ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ” G-Power TikTok Creative Award ” በሰተኘ ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥነ-ምግባር  ባፈነገጠ አኳሃን ሰውነታቸውን የገላለጠ አለባበስ ለብሰው በአደባባይና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የታዩ

ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማጣራት መጀመሩን አስታውቋል። ‎

ሰሞኑን በተካሄደው ዝግጅት ላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ባህል እና መልካም ሥነ-ምግባር በተቃራኒ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ እና በቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት የታዩ፣ ዝግጅቱን በስፖንሰርነት የደገፋ እና ፕሮግራሙን ያቀነባበሩ ተጠርጣሪዎች ወንጌላዊት ገብረ እንድርያስ በርሄ፣‎ በርከት ፀጋዬ ጅፋር፣‎ መቅድም ደረጄ መንግስቱ፣‎ ግሩም ገዛሀኝ ቀጭኔ እና‎ ዮሃንስ መኮንን ሀ/ማርያም ‎የተባሉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቀጥጥር ስር  ያዋላቸው መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ” ከህብረተሰቡ ባህልና እሴት ያፈነገጡ አለባበሶችና መጤ ባህሎች ተስፋፍተው በትዉልዱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳያስከትሉ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የጀመርነውን ምርመራ አጠናክረን እንቀጥላለን ” ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates