ማህበራዊ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ2026 የእርዳታ ጥያቄውን ማቋረጡ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/03/2018- የተባበሩት መንግስታት የገንዘብ ድጋፍ በ10 ዓመት ውስጥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ። ከሚጠበቀው መጠን ገንዘብ 1/3 ያነሰ እንደሆነም ተገልጿል።

ጋዛ፣ ሶሪያ እና ሱዳን በ2026 ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ እየተገለፀ ባለበት ጊዜ የተመድ የያዘው በጀት በጣም እንደቀነሰ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትናንት ሰኞ ዕለት ይፋ እንዳደረገው የ2026 የእርዳታ በጀት በዚህ አመት ከተጠበቀው ግማሽ ያህሉን መሆኑ የገለፀ ሲሆን የለጋሾች የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ በተለይ ደግሞ የአሜሪካ ድጋፍ መቆም መሆኑ አምኗል።

ይህ የድጋፍ ማሽቆልቆል የ23 ቢሊዮን ዶላር አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን እንደሚጎዳ ጠቅሷል።

የገንዘብ ቅነሳው በግጭት ቀጠናዎች ውስጥ ባሉ ሰራተኞች ላይ የደህንነት ስጋቶችን እና የመዳረሻ እጥረትን ጨምሮ ለእርዳታ ኤጀንሲዎች ከሚያጋጥሟቸው ሌሎች ተግዳሮቶች በተጨማሪ ምክንያትነት አስቀምጧል።

የተባበሩት መንግስታት ‘ፈታኝ፣ አስቸጋሪ፣ ጨካኝ ምርጫዎችን’ እያደረገ ነው ብሏል። “እነዚህን ፈታኝ፣ አስቸጋሪ፣ ጨካኝ ምርጫዎች እንድናደርግ የሚያስገድዱን የእርዳታ ቅነሳዎች ናቸው” ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ኃላፊ ቶም ፍሌቸር ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

“ከመጠን በላይ ተወጥረናል፣ በቂ ገንዘብ አናገኝም እና ጥቃት ይደርስብናል” ብለዋል።

ከአንድ አመት በፊት የተባበሩት መንግስታት ለ2025 ወደ 47 ቢሊዮን ዶላር ይፈልግ የነበረ ሲሆን ይህ አሃዝ በኋላ ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና እንደ ጀርመን ያሉ ሌሎች ከፍተኛ የምዕራባውያን ለጋሾች የእርዳታ ቅነሳ መጠን ብቅ ማለት ሲጀምሩ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።

የህዳር ወር አሃዞች እንደሚያመለክቱት እስካሁን 12 ቢሊዮን ዶላር ብቻ እርዳታ የተገኘ ሲሆን ፣ ይህም በ10 ዓመታት ውስጥ ዝቅተኛው ነው ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates