ዲፕሎማሲ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሳውዲ አረቢያ ገቡ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/03/2018- ፕሬዝዳንቱ በንጉሥ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ አል ሳዑድ ግብዣ መሰረት ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ለአራት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዳቀኑ የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል አስታውቋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ልዑካቸው በአራት ቀናት ቆይታቸው ወቅት ከሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ የትብብር እና የአጋርነት ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ እና አለም አቀፍ የጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብሏል ሚኒስትሩ።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኢሳያስ ወደ ሪያድ ያቀኑት የዓሰብ ወደብን ለሳውዲ መንግስት ለመስጠት እንደሆነ ነው።

በዚህም ከሳውዲ ዓረቢያ መንግስት የተለያዩ ስምምነቶች ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የቀይ ባህር በር ላለመቀበል እያንገራገረ የሚገኘው የኤርትራ መንግስት ከግብፅና ከሳውዲ ዓረቢያ ጥብቅ ግንኙነት ፈጥሮ እየሰራ እንደሚገኝ ይገለፃል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባለፈው ወር ወደ ካይሮ በማምራት ከግብፅው ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ለአምስት ቀናት የቆዩ ሲሆኑ ከአንድ ሳምንት በፊት ደግሞ ወደ ፖርት ሱዳን በማቅናት ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልቡርሃን እንደቆዩ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ለአራት ቀናት ወደ ሳውዲ ማምራታቸው ተገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates