ፖለቲካ

በቤኒን የተሞከረው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት መክሸፉ ተገለጸ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/03/2018፡- እሁድ ማለዳ የቤኒን ጦር ሠራዊት አባላት ሥልጣን መያዛቸውን ያስታወቁበት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መክሸፉን እና ፕሬዝዳንቱ በደኅና ሁኔታ በፈረንሳይ ኤምባሲ ውስጥ አንደሚገኙ የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።

የቤኒን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ውስጥ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት መክሸፉን አስታውቀዋል።

ቀደም ሲል በሌ/ኮሎኔል ፓስካል ቲግሪ የሚመራ የወታደሮች ቡድን በቴሌቪዥን ባስተላለፈው መልዕክት ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎንን ከሥልጣን አስወግዶ የአገሪቱን ሕገመንግሥት ማገዱን አስታውቆ ነበር።

ሆኖም የቤኒን ፕሬዝዳንት አማካሪ ፕሬዝዳነቱ በደህና ሁኔታ ፈረንሳይ ኤምባሲ ውስጥ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

“ዛሬ እሁድ ማለዳ ላይ ትንሽ ቁጥር ያላቸው የወታደሮች ቡድን የአገሪቱን መንግሥት እና ተቋማትን ለማናጋት የአመጽ ተግባር ፈጸሟል” ሲሉ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው መክሸፉን የቤኒን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አላሳኔ ሴይዱ አስታውቀዋል።

የመፈንቅለ መንግስቱ ሙኮራ ተከትሎ ጉዳዩን ያስተባበሩት 12 ከፍተኛ መኮንኖች የሚገኙበባቸው 13 አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው እየተገለፀ ይገኛል።

ሙኮራውን የአፍሪካ ሕብረት በፁኑ አውግዞታል። የምዕራብ አፍሪካ ማሕበረሰብ ድርጅት ኢኮዋስ ደግሞ ልዩ የጥምር ሐይል ወደ ቤኒን እንደላከ ታውቋል።

በአፍሪካ መፈንቅለ መንግስት እየተለመደ የመጣ ሲሆን ባለፈው ሳምንትም በጊኒ ቢሳዎ ተመሳሳይ ተግባር መፈፀሙ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates