ኢኮኖሚ
19ኛው የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የብሔራዊ ስታትስቲክስ የዳይሬክቶሬት ጀነራል ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/03/2018፡ ስብሰባው ‘ፍትህና ካሳ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ አፍሪካ’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በስብሰባው እንዳሉት፥ ኢትዮጵያ ቀርጻ ወደ ትግበራ ያስገባቻቸው የልማት ግቦችና ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተዓማኒ መረጃ ይፈልጋሉ ብሏል።
ተአማኒ ስታትስቲክስ እና ልማት ተነጣጥለው እንደማይታዩ ጠቅሰው፥ ስታትስቲክስ መረጃን መሠረት ላደረገ ጠንካራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል።
የዘርፉን ሚና ለማጎልበት ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋም መገንባት፣ ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ መፍጠር እና አኅጉራዊ ትስስርን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
እውነተኛ የስታትስቲክስ መረጃ እንደ ሀገር ሆነ እንደ አኅጉር የት እንደቆምን የማሳየት አቅም አለው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኢትዮጵያ ዘርፉን ማዕከል ላደረጉ አኅጉራዊ ትግበራዎች ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።



