ዲፕሎማሲ
አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ታጠናክራለች ሲሉ የአሜሪካው አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋን ተናገሩ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/03/2018፡ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቁርጠኛ ናት አሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ሀገራቱ በፖሊስ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል
እንዲሁም በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ እና በሌሎች በዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት አላት፡፡
በተለይም ዋሽንግተን ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ነው ያረጋገጡት፡፡



