ማህበራዊ
በዓለም ዙሪያ ከ1 ቢሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች እንዳሉም ተገለጸ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/03/2018፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች ሙሉ ተሳትፎ እና ጥቅም ከሌለ ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ አይቻልም ሲል ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በዓለም ላይ በማኅበራዊ ለውጥ ውስጥ ግዴታቸውን የሚወጡ የአካል ጉዳተኞች፤ በፈጠራ መስክን ይሰራሉ መምራትም ይችላሉ ያለው መግለጫዎ፤ ምንም እንኳን በፖሊሲ ቀረጻ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ቢያሳድሩም፤ በውሳኔ አሰጣጥ ቦታዎች እና መዋቅሮች ውስጥ እንዲመሩ በማረጋገጥ ረገድ ተገሏል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበዓሉ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የአካል ጉዳተኞች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ ዛሬ እየተከበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የስራ ሐላፊዎች በተገኙበት በውይይት ተከብሯል።



