ጤና

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40.8 ሚሊዮን መድረሱ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/03/2018፡- የዓለም ጤና ድርጅት ለዘርፉ የገንዘብ ድጋፍ በቀነሰበት ወቅት ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከተጠቀሰው ቁጥር 64 በመቶ በአፍሪካ እንደሆነ አስታውቋል።

እ.አ.አ. በ2024 መጨረሻ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ 40.8 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ የተያዙ ሲሆን ከ64% በላይ የሚሆኑት ደግሞ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ይገኛሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ አሃዝ አመልክቷል።

ድርጅቱ የገንዘብ ቅነሳ አገልግሎቶችን እያስተጓጎለ እና ኤድስን እንደ የህዝብ ጤና ስጋት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት ስጋት መሆኑን አስጠንቅቋል። መረጃው የወጣው ታህሳስ 1 ቀን 2025 በተከበረው የዓለም የኤድስ ቀን ላይ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው የአፍሪካ አህጉር 26.3 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ የተያዙ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ በ2024 ዓመት 650,000 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ ስያዙ 380,000 በበሽታው እንደሞቱ አመልክቷል።

በተጠቀሰው ተመሳሳይ ዓመት በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ የተያዙ ሲሆን 630,000 ደግሞ በኤችአይቪ ምክንያት ሞተዋል። ሆነም ድርጅቱ ከ2010 ጀምሮ አዳዲስ ኢንፌክሽኖች በ40% ቀንሰዋል፣ ሞት ደግሞ በ54% ቀንሷል ሲል አስታውቋል።

 

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates