ፖለቲካ

ፑቲንና የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ በዩክሬን ጉዳይ ለመምከር ዛሬ በሞስኮው እንደሚገናኙ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/03/2018፡- የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካው አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ጋር ዛሬ ማክሰኞ በሞስኮው እንደሚገናኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህ የሞስኮው ጉዞ የተሰማው ነጩ ቤተ መንግስት በሩስያና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ከስምምነት ለመድረስ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች መኖራቸውን ከተናገረ በኋላ ነው፡፡

የሞስኮው ቀጠሮ አስቀድሞ ለሩስያ ያደላል በተባለው የአሜሪካ የሰላም አማራጭ ስምምነት ዙሪያ የዩክሬንና ዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በፍሎሪዳ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የፍሎሪዳውን ውይይት ገንቢ ሲሉ ቢገልጹትም ተጨማሪ ሥራዎችን የሚፈልጉ አስቸጋሪ ጉዳዮች መኖራቸውን ግን አልሸሸጉም፡፡

ትናንት ሰኞ ከፈረንሳዩ አቻቻው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ከተወያዩ በኋላ ቃላቸውን የሰጡት ዘለንስኪ ኪየቭ በሰላም ንግግሩ ዙሪያ ቅድሚያ የምትሰጠው ሉዓላዊነቷንና ጠንካራ የደኀንነት ዋስትና ማግኘትና ማስቀጠል መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዝደንቱ ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ንግግር የግዛት ጉዳዮች እጅግ አስጋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ክሬምሊን በምስራቃዊ የሀገራቸው ክፍል የተቆጣጠራቸው ስፍራዎችን መጠቅለል ትፈልጋለች፤ ኪየቭ ግን መቼም አታደርገውም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates