ዲፕሎማሲ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ የሱዳን የሰላም ሁኔታ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት እንደሚደግፉ አረጋገጡ።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በፖርት ሱዳን ጉብኝት አድርጓል።

ኢትዮ ሞ ኒተር፡ 22/03/2018፡- የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ኃላፊ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቅዳሜ ዕለት በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እየጨመረ በመጣው አለመረጋጋት መካከል የስትራቴጂካዊ ጥምረት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ከሉዓላዊ ምክር ቤቱ የተሰጠ መግለጫ እንዳመለከተው መሪዎቹ “የጋራ ትብብርን ስለማነቃቃት” እና ቀጠናዊ የፀጥታ ሁኔታን ገምግመዋል።

አል ቡርሃን አስመራ ለሱዳን ሉዓላዊነት ያላትን ድጋፍ በማድነቅ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን “ስትራቴጂካዊ” ሲሉ መግለፃቸው ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ለሱዳን አንድነት ያላቸውን ድጋፍ በማረጋገጥ “የውጭ ጣልቃገብነቶችን” ውድቅ አድርገዋል።

ፕሬዝዴንት ኢሳያስ አፍወርቂ ወደ ፖርት ሱዳን ያደረጉት ጉብኝት እ.ኤ.አ. በ2019 ኦማር አል-በሽር ከተወገዱ በኋላ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ጄኔራል አልብሩሀንን ጨምሮ የሱዳን የጦር መኮንኖች ለፕሬዝደንት ኢሳያስ በፖርት ሱዳን ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ሌተናል ጄኔራል አልብሩሀን በፈገግታ ታጅበው ከፕሬዝደንት ኢሳያስ ጋር በሚጓዙበት ወቅት የሱዳን የጦር መኮንኖች አንድ እጃቸውን ጨብጠው ወደላይ በማንሳት የድል ምልክት ሲያሳዩም ታይቷል፡፡

በሌላ የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሐላፊ አልቡርሃን ወደ ፖርት ሱዳን የገቡት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ የግል መልእክተኛ ራምቴን ላማምራን ተቀብሎ አነጋግሯል።

የሱዳን የጦር አዛዥ አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን መንግስት በመላ አገሪቱ ሰላም ማስፈን እንደሚፈልግ ተናግሮ፤ ነገር ግን ማንኛውም ድርድር ከመጀመሩ በፊት ተቀናቃኛቸው ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሉ ከተቆጣጠራቸው አካባቢዎች መውጣት አለበት ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates