የተለያዩ
በመቐለ ከተማ የቦምብ ፍንዳታ ማጋጠሙ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/03/2018፡- በዓዲ ሃቂ ክፍለ ከተማ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ግቢ አጠገብ ያጋጠመው የቦምብ ፍንዳታ በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ የከተማዋ የሰላምና ደህንነት ዘርፍ ጽ/ቤት ገልጿል።
የከተማዋ የሰላምና ደህንነት ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ረድሀኝ ፍስሃ ለ104.4 FM ሬድዮ እንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈጸመው ትላንት ከምሽቱ 4፡25 አካባቢ ነው።
በሰው ህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፤ ሆኖም ግን ብዙ ሰዎች በፍንዳታው ድምፅ ተደናግጠዋል፤ የከተማዋ ህዝብ ይህንን ተረድቶ የሽብርተኝነትን ተግባር ማውገዝ አለበት ብሏል። ሆኖም መረጃዎች እንደሚያሳየው በንብረት ላይ የተወሰነ ጉድአት እንደደረሰ ነው።
ፍንዳታው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ነው ያሉት ሐላፊው የክልሉ እና የከተማ የፀጥታ እና ደህንነት አካላት ወንጀለኞቹን ለመያዝ በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን አክለዋል።
በከተማዋ ውስጥ ሆን ተብሎ ከተፈፀመው ፍንዳታ በስተቀር ሌላ ምንም ነገር አልተከሰተም፤ ህዝቡም ተረጋግቶ በአካባቢው ያለውን ደህንነት መጠበቅ እንዳለበት አሳስቧል።
የፍንዳታው ዓላማ ማን ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ በፅ/ቤቱ ባይገለፅም በከፍተኛ የፀጥታ አመራሮች እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።



