
ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/03/2018፡- ግለሰቡ በጂንካ ከተገኘው የመጀመሪያው የማርበርግ ቫይረስ ተጠቂ ጋር ንክኪ የነበረው ወደ አካባቢው ተጉዞ ወደ ሃዋሳ ተመላሽ የነበረ ነውም ተብሏል።
ይህ የተባለው የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ እየሰሩት ያለውን ስራ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግልጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ቫይረሱ ከተከሰተበት ከህዳር 5 ቀን እስከ ህዳር 17ቀን 2017ዓ.ም ድረስ 73 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገዋል ያለው የጠየና ሚኒስቴር በዚህም 11 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ 7ቱ ህይወታቸው አልፏል፤ 5ቱ ደግሞ በህክምና ላይ ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።
349 ግለሰቦች ንክኪ ያላቸው በመሆኑ ክትትል እየተደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 119ኙ የለይቶ ማቆያ ጊዚያቸውን ማጠናቀቃቸውን መረጃዉ አሳይተዋል።
ይህን ገዳይ ቫይረስ ለመቆጣጠር እንዲሁም በበሽታው ላለመያዝ የመተላለፊያ መንገዶቹን እና ሊደረጉ የሚገባ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ባለሞያዎች ይመክራሉ።



