ዲፕሎማሲ
ኢትዮጵያ የመከላከያ ዘርፈዋን ለማጠናከር ከፈረንሳይ እና ኳታር መወያየትዋ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 18/03/2018፡- የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በዲፕሎማሲያንና መከላከያን በማጠናከር ዙሪያ መወያየታቸው ተገልፀዋል።
ሚኒስትር አይሻ መሀመድ በኳታር ዶሃ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
በትላንትናው ዕለት የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከሆኑት ሼክ ሳኡድ ቢን አብዱራህማን ቢን ሀሰን አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ተብለዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በጄኔራል ፒየር ሺል የተመራ የፈረንሣይ ወታደራዊ ልዑክ ከኢፌዴሪ መከላከያ አመራሮች ጋር ትላንት መምከሩ ተገልጿል።



