አፍሪካ

የሱዳን የሲቪል ኃይሎች ጥምረት የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች የሦስት ወር የጦርነት ማቆም ውሳኔን እንደሚደግፍ ኣስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/03/2018፡- የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሓይሎች መሪ ጄነራል መሓመድ ዳጋሎ እንዳስታወቁት በተናጠል የወሰዱት እርምጃ የሲቪል ዜጎችን ጥበቃ ለማሳደግ እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ነው ብለዋል።

ይህ ታሪካዊ ውሳኔ ነው በማለት የገለፀው የሲቪል ኃይሎች ጥምረት ሕዝቡ በጦርነት እና በግጭት ውድመት እያጋጠመ ባለበት ወቅት መሆኑ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት እውነተኛ እርምጃን ነው ብሎ እንደሚያምን ኣስታውቀዋል።

መግለጫው የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን እና የሱዳንን ሕዝብ ስቃይ ለማቃለል ከልብ እንደሚጥሩ መግለጻቸው የሰብአዊነት እሴቶች እውነተኛ ተምሳሌት ሆኖ እናያለን ሲልም ውሳኔውን አሞካሽተዋል።

የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች የሰብአዊ ስምምነት ማወጃቸው በጦርነት ጨለማ ውስጥ የተስፋ ምልክት ሲሆን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እውነተኛ ቁርጠኝነትን ያሳያል ብለዋ።

ይህ በእንዲህ እያለ የሱዳን ሚኒስትሮች ምክር ቤት የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ የወሰነውን የተኩስ አቁም የተናጠል ውሳኔ እንደማይቀበለውና ጦርነቱ በሚጠቁም መልኩ በጄነራል አልቡርሃን ለሚመራ የሱዳን ሰራዊት ድጋፉን አረጋግጠዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates