የአየር ንብረት አካባቢ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጢሞቴዎስ የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት በመሆን በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መመደባቸው ታውቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/03/2018፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት እንዳስታወቀው በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መድቧል።
ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን እንደሚመሩም ያስታወቀው መረጃው የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋናውን በማቅረብ በዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አስተባባሪነት ከአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል ብሏል።



