አፍሪካ

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የአልሸባብ አባላትን የብሔራዊ መታወቂያ እንድያገኙ መመሪያ መስጠቱን ተናገሩ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 17/03/2018፡- የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ አክራሪው የአልሸባብ ቡድን አባላቱን ለአገሪቱ አዲስ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ እንዲመዘገቡ እንዳዘዘ አስታውቋል።

ሐሰን ሼክ የመታወቂያ ስርዓቱን ስለማስተዋወቅ በተደረገው ስብሰባ ላይ ሲናገሩ፣ ውሳኔው በደስታ እንደሚቀበሉት በመግለፅ፣ የባዮሜትሪክ ምዝገባ ባለስልጣናት በሽብርተኝነት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ለመለየት እንደሚረዳ አመልክቷል።

“የጣት አሻራቸው እና ፊታቸው ይታወቃል፤ ይህም አሸባሪ የሆኑ የሶማሊያ ዜጎችን ለመለየት ይጠቅመናል” በማለት ተናግሯል።

ፕሬዝዳንት ሞሃመድ እንዳሉት የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራሙ ደህንነትን ያጠናክራል፣ ኢኮኖሚውን ያሳድጋል እንዲሁም ሽብርተኝነትን፣ የገንዘብ ዝውውርን እና ሌሎች ወንጀሎችን ለመግታት ይረዳል።

ወንጀለኞች ወደ ውጭ አገር እንዳይጓዙ እና ለሌሎች አገሮች አደጋ እንዳይፈጥሩ ለመከላከልም እንደሚረዳ አስታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates