የተለያዩ

በአዲስ አበባ በቡድን በመደራጀት ወንጀል ሲፈፀሙ ነበሩ የተባሉት 36 ግለሰቦች መያዛቸው ተገለፀ፡፡

ለወንጀር ተግባር ይውሉ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብለዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/03/2018፡- በአዲስ አበባ ከተማ በቡድን በመደራጀት በተለምዶ “ሿሿ” ተብሎ የሚጠራውን ወንጀል የሚፈፅሙ እና ከወንጀለኞቹ የተሰረቀ እቃን የሚገዙ 36 ግለሰቦች ከ5 ተሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቀዋል፡፡

የከተማዋ ፖሊስ በማሕበራዊ ሚድያ ገፁ ባሰራጨው መልዕክት የምርመራ መነሻ የሆነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኤሚግሬሽን አካባቢ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ላይ የተፈፀመ የወንጀል ድርጊት መሆኑን ገልጿል።

ይህም የግል ተበዳይ የሆኑት ኢየሩስ ግርማ የተባሉት ግለ ሰብ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳሉ ወንጀል ፈፃሚዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ማ.ኢ 01058 ሚኒባስ ተሽከርካሪ ይዘው በመንቀሳቀስ የት ነሽ? በማለት ካሳፈሯቸው በኋላ ሞባይል ስልካቸው ለመቀማት ሲታገሉ በአካባቢው ላይ በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ዕይታ ውስጥ መውደቃቸውን አስታውሷል።

በፖሊስ ዕይታ ውስጥ መውደቃቸውን የተረዱት ተጠርጣሪዎችም የግል ተበዳይን ገፍትረው በመጣል ለማምለጥ ቢሞክሩም ተጠርጣሪዎቹን እስከ መጨረሻው በመከታተል አራቱንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋሉትን ተጠርጣሪዎች መነሻ በማድረግ በተደረገ ምርመራ የማስፋት ተግባር የወንጀል ድርጊቱን የሚመራ እና የሚያስተባበር ቡድን መኖሩን እንደተደረሰበት ተጠቁሟል፡፡

ከወንጀል ፈፃሚዎች የተሰረቀ እቃ ሲገዙ የነበሩ ሁለት የሌባ ተቀባዮች ተይዘው በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ እና ፍተሻ ከግለሰቦቹ መኖሪያ ቤት 30ሺ 700 ብር፣ 1 ላፕቶፕ፣ 1 ታብሌት፣ 11 ዘመናዊ ስልኮች፣ ተሰርቀው ቀፎዎቹ የተሸጡበት 188 የስልክ ከቨሮች በኤግዚቢትነት መያዙ ተጠቁሟል።

በአጠቃላይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ 36 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንም ፖሊስ መምሪያው አመልክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates