አፍሪካ

የስዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ሐይል አዛዥ ጄነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ለሦስት ወራት የሚቆይ የተናጠል የሰብአዊ እርዳታ ስምምነት ማድረጋቸው ገለፁ፡፡

ተቀናቃኛቸው ጄነራል አልቡርሃን የሰላም ስምምነት ምክረ ሐሳቡ እንደማይቀበሉት መግለፃቸው ይታወቃል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 16/03/2018፡- የሱዳን ፈጣን የድጋፍ ኃይሎች አዛዥ ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ትላንት በይፋ እንዳስታወቁት ለሦስት ወራት የሚቆይ የተኩስ ማቆምን የሚያካትት የሰብአዊ ስምምነት መድረሳቸወን አስታውቀዋል።

ይህም ጦርነቱን ለማስቆም በመስከረም 12 በኳድ ጥምረት አገራት ጦርነቱን ለማስቆም የቀረበውን ምክረ ሐሳብ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ነው ተብለዋል። እነዚህም ወደ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት እና ግልጽ የሆነ የሽግግር ሂደት ለማምጣት የታሰበ የመጀመሪያ የሦስት ወር የተኩስ አቁም ስምምነትን እንደሚያካትት ተጠቁመዋል።

“በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሚመራው ዓለም አቀፍ ጥረቶች ምላሽ ለመስጠት፣ ፈጣን ድጋፍ ሐይሉ እና አጋሮቹ የሶስት ወር የተኩስ አቁም ስምምነት እና ወታደራዊ እርምጃዎችን ለማስቆም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን እናሳውቃለን” ሲሉ ሄሜቲ በቪዲዮ የተቀረፀ ንግግራቸው ተመልክተዋል።

“ታሲስ” በሚል የሚጠራውን ትዩዩ መንግስት ጥምረት የሚመሩት ዳግሎ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እና የሰብአዊ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

የእርዳታ ስራዎችን ለማመቻቸት፣ የሰብአዊ ሰራተኞችን ደህንነት እና ወደ ሁሉም የተጎዱ አካባቢዎች ያለ ምንም እንቅፋት መድረስን ለማረጋገጥ ቃል ገብተዋል።

ዳግሎ በሲቪሎች ላይ በተፈጸመው በደል የተሳተፉትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውም አረጋግጠዋል። ሙያዊ ምርመራዎች እየተካሄዱ መሆናቸውን እና ፍትህ በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት እንደሚፈጸም ተናግረዋል።

ዳግሎ የተኩስ አቁም እርምጃው ለችግሩ አጠቃላይ የፖለቲካ መፍትሄ ለማድረግ የመጀመሪያ እርምጃ እንደሆነ በመግለፅ የእስላማዊ ንቅናቄን እና የብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲን ሳይጨምር ሁሉንም ፓርቲዎች የሚያካትት የፖለቲካ ውይይት ላይ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

ጄነራል ዳጋሎ ይህን ያስታወቁት የሱዳኑ ጦር መሪ ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በአሜሪካ የቀረበውን የሰላም ምክረ ሐሳብ እንደማይቀበሉት በገለፁበት ማግስት ነው፡፡

ጄነራል አልቡርሃን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ የሚትገኝበት ዕርቅ ተቀባይነት የለውም በአሜሪካ የቀረበው ሰነድም የኢሚሬትስ ፍላጎት ማስፈፀሚያ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡
የሱዳን ሰራዊት ኤልፋሻርን ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሊ ነፃ ለማውጣት እየገሰገሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates