ኡጋንዳ ዛሬም ለዘለአለምም በሰላማዊ እና በመከባበር በር ባህር የማግኘት መብት አላት ሲሉ የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አረጋገጡ።
ኡጋንዳ እና ኬኒያ ወደ ግጭት ለማስገባት የሚመኩሩ አካላትም ተውን እረፍት ስጡን ብሏቸዋል።

ኢትዮሞኒር፡ 15/03/2018፡- የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኡጋንዳ በነበራቸው ጉብኝት እንደተናገሩት ❝…ኬንያ እና ኡጋንዳ ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው።
ኡጋንዳ የሕንድ ውቅያኖስን እንድትጠቀም የመንገድ፣ የባቡር እና የፈሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦ ዝርጋታ ስራችንን እያፋጠንን እንገኛለን። በሕንድ ውቅያኖስ አጠቃቀም ዙሪያ እንድንጋጭ¹ ለሚፈልጉ ያለኝ መልእክት ‟እረፍት ስጡን” የሚል ነው ብሏል።
ቀጠናው እድገትና ብልፅግናን እንዲጋራ ኡጋንዳና ሩዋንዳን ጨምሮ ከሁሉም ሀገራት ጋር በትብብር መስራታችንን እንቀጥላለን። እኛ ብልፅግናን እንጂ ድህነትን መጋራት አንፈልግም…❞ ሲሉም ተደምጧል ዊልያም ሩቶ።
ፕሬዝዳንት ሩቶ ይህን ያሉት ከዚህ በፊት የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሶቬኒ ባህር አልባ አገሮች በር ማግኘት ካልቻሉ ጦርነት ሊያስነሱ ይችላሉ ማለታቸው ተከትሎ ነው።
ፕሬዝዳንት ሙሶቬኒ ኡጋንዳ የበር ባህር እንድትጠቀም ኬኒያን በተደጋጋሚ እንደጠየቀች በማስታወስ ነገር ግን በጎ ምላሽ እንዳላገኘች በቅሬታ ገልጿል።
ይህን ተከትሎ የአገሪቱ የጦር መሪ የሙሶቬኒ ልጅ አባቴ ከፈቀደልኝ ኬኒያን በሰዓታት መቆጣጠር እችላለሁ ብሎ መዛታቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ ግን ኡጋንዳ በሰላማዊ መንገድ የበር ባህር ማግኘት እንደምትችል በማረጋገጥ ዕድገት እና ልማት እንጂ ጦርነት አያስፈልገንም ብሏል።
የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ንግግር የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሶቬኒ ‟የሕንድ ውቅያኖስ የእኔ ነው” ማለታቸውን ተከትሎ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረውን የነበረውን የቃላት ጦርነት እንደሚያለዝበው ይጠበቃል።



