መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል ከወራት በኋላ በቤይሩት በፈፀመችው አዲስ ጥቃት ከፍተኛ የሔዝቦላህ ባለሥልጣን መግደሏን ተገለፀ።

ኢትዮሞኒር፡ 15/03/2018፡- የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በፈጸመው ጥቃት ነው የሔዝቦላህ ከፍተኛ ባለሥልጣን መግደሏ የተገለፀው።

የተገደሉት ባለሥልጣን የሔዝቦላህ ዋና ኢታማዦር ሹም ሀይታም አሊ አል ታታባይ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ቡድኑን በተለያዩ ከፍተኛ የሥልጣን እርከኖች ላይ ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር፤ በዳሂ ዲስትሪክት የመኖሪያ ህንጻ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ አምስት ሰዎች መገደላቸውን እና 28 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።

ሔዝቦላህ የታታባይን ሞት አረጋግጦ፣ እስራኤል ጥቃቱን በመፈጸም “ቀይ መስመር” አልፋለች ብሏል።የእስራኤል ጦር ከወራት በኋላ በደቡባዊ ቤይሩት ጥቃት ሲፈጽም ይህ የመጀመርያው ነው።

ባለፈው ኅዳር ወር በዩናይትድ ስቴትስ እና በፈረንሳይ አደራዳሪነት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል በኢራን ከሚደገፈው ሔዝቦላህ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን ሰዎች እና ተቋማት ማጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።

የእስራኤል ባለሥልጣናት ሔዝቦላህ ወታደራዊ አቅሙን ዳግም ለማጠናከር እየሞከረ ነው በማለት ይከስሳሉ።

አክለውም የጦር መሣሪያ ወደ ሊባኖስ እያስገባ እና በሮኬቶች እና ሚሳዔሎች ምትክ የሚፈነዱ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እያመረተ መሆኑን በመጥቀስ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ይገልጻሉ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከጥቃቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ “በእኔ መሪነት የእስራኤል መንግሥት ሔዝቦላህ አቅሙን መልሶ እንዲያጠናክር፤ በእስራኤል መንግሥት ላይም ስጋት እንዲፈጥር አንፈቅድም” ብለዋል።

የሊባኖስ መንግሥት “ሔዝቦላን ትጥቅ ለማስፈታት የገባውን ግዴታ ይፈጽማል” ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates