አሜሪካ የሱዳኑን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል እያስታጠቀች ያለችውን አገር ማን እንደሆነ ታውቃለች ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ተናገሩ፡፡
ድርጊቱ መቆም እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/03/2018፡- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ መንግስታቸው የሱዳንን ፈጣን የድጋፍ ኃይሎችን መሳሪያ የሚያቀርበው ማን እንደሆነ ያውቃል እና ይህ ድጋፍ መቆም እንዳለበት ቢናገሩም እናውቃታለን ያሉዋት አገር ግን ማን እንደሆነች በስም አልጠሩም፡፡
በካናዳ በተካሄደው የቡድን 7 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ መጨረሻ ላይ ለጋዜጠኞች የተናገሩት ሩብዮ “RSF የሚያገኘውን መሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎች ለማቆም አንድ ነገር መደረግ አለበት” ብለዋል።
“አንድ ሰው ገንዘቡን እየሰጣቸው ነው፣ አንድ ሰው ደግሞ መሳሪያውን እየሰጣቸው ነው፣ ይህም ከተወሰኑ ሀገሮች ነው እየመጣ ያለው” ብለዋል።
“ማን እንደሆኑ እናውቃለን፣ እናም ስለሁኔታው እናነጋግራቸዋለን፤ ይህንን ማስቆም ካልቻልን በእነሱ ላይ እና በዓለም ላይ መጥፎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እንዲረዱ እናደርጋለን።” ሲሉ ተደምጠዋል ማርኮ ሩብዮ፡፡
ሩቢዮ እንዳሉት በሱዳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎችን የገደለ እና 13 ሚሊዮን ሰዎችን ከቀያቸው ያፈናቀለው ጦርነት በቡድን 7 ስብሰባ ላይ ከብዙ አገሮች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት እንደተደረገበት እና ችግሩን ለመፍታት በመንግሥታቸው ከፍተኛ ጥረት እየተደረገበት መሆኑ ገልፀዋል፡፡
ጨምረውም “ተሳታፊዎቹ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን፣ ለዚህም ነው ከሌሎች የተሳተፉ ሀገራት ጋር በመሆን የኳድ አካል የሆኑት” ሲሉ ሩቢዮ ተናግረዋል። በአሁን ጊዜ አሜሪካን ጨምሮ ግብፅ፣ ሳውዲ ዓረቢ እና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ የካድ ቡድን ፈጥሮ በሱዳን ለሶስት ዓመታት የቀጠለውን ጦርነት ለመፍታት ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ሽምዋ በይጠቀስም የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል ትደግፋለች እየተባለች ያለቸው ግን ኢሚሬትስ ነች፡፡ “ያዘጋጀነውን የኳድ ሂደት ሰዎች ‘እሺ፣ ከኳድ ጋር ተሳትፈናል፣ ለመፍታት እየሞከርን ነው’ ብለው የሚደብቁበት እንግዳ እንዲሆን አንፈቅድም” ሲሉም ማርኮ ሩብዮ አፀነኦት ሰጥተዋል፡፡



