የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ነው ሲል ዓለም አቀፉ ድርጅት ጄኖሳይድ ዎች አስታወቀ።
የሻዕቢያ ባለስልጣናት በትግራይ ለፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀልም በዓለም አቀፉ የወንጀሎች ፍርድ ቤት እንዲጠየቁ ጠይቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/03/2018፡- ጄኖሳይድ ዎች የተሰኘ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተዉ የኤርትራ ስርዓት ሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከማፈን ባለፈ በገዛ ዜጎቹ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ነው ይላል።
ከዚህ በፊት የቡድ 11 የሚባሉ ፖለቲከኞች እና ከ16 በላይ ጋዜጠኞች በስርዓቱ ታፍኖ የደረሱበት እንደማይታወቁ የገለፀው ሪፖርቱ ገደብ የሌለው ብሄራዊ አገልግሎትን ጨምሮ በእምነቶች እና በአናሳ ብሄረሶቦች የሚፈፀመውን ወንጀል የኤርትራ ህዝብ ቁጥር እንድያሽቆለቁል እንዳደረገው ገልፀዋል።
አሜሪካ ወይም ማንኛውም የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገር በትግራይ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICJ) እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
”የኤርትራ ሪፖርት 2025” የሚል ርዕስ የወጣው እና በጄኖሳይድ ዎች ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ ላይ የታተመው ዘገባ የኤርትራ ኃይሎች የትግራይን ጦርነት በይፋ ያቆመውን የ2015 የሰላም ስምምነት ቢያደርጉም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸውን ቀጥለዋል ብሏል።
የዘር ማጥፋት ወንጀል ኤርትራ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሃት መካከል በተደረገው የሰላም ስምምነት ውስጥ እንዳልተሳተፈች አስታውሶ በአሁኑ ጊዜ ሰራዊቷ ከትግራይ እንድታስወጣ እና ስምምነቱን እንድትፈርም አሳስቧል።
ኤርትራ በትግራይ ላይ በተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፋለች ሲል ሪፖርቱ በመግለፅ፣ እስከ ዛሬ ድረስ ወታደሮቿ በትግራይ ምድር መኖራቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው አለመረጋጋት አንዱ ምክንያት እንደሆነ አክሏል።
በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ወደ ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።



