አፍሪካ

ተመድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሱዳን እየተፈጸመ ያለውን “አሰቃቂ ግፍ” ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/03/2018፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ፣ በሱዳን ኤል-ፋሸር እየተፈጸመ ያለውን “አሰቃቂ ግፍ” ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ በማሳሰብ፤ ዓለም የዘር ማጥፋት ወንጀል እስኪታወጅ ድረስ መጠበቅ የለባትም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ ከሱዳን መንግስት ሰራዊት ጋር በጦርነት ላይ የሚገኘው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል፣ በቅርቡ በምዕራብ ዳርፉር የምትገኘውን የመጨረሻዋን ወታደራዊ ምሽግ ኤል-ፋሸርን መቆጣጠሩ ይታወሳል።

ቡድኑ ከ18 ወራት ከበባ በኋላ ኤል-ፋሸርን መቆጣጠሩን ተከትሎ ዘር ተኮር ግድያዎችን ጨምሮ የሰዎች እገታና ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊቶች መፈፀሙን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልፀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ከኤኤፍፒ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሰቃቂ ወንጀሎች እየተፈጸሙ መሆናቸው ግልጽ ነው “፤ ከበባው ራሱ “አሰቃቂ ወንጀል” ነበር ብለዋል፡፡

“ሰዎች ከበባ ውስጥ በነበሩበት ወቅት አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ይኖሩ ነበር” ያሉት ኮሚሽነሩ “ምግብ እና ውሃ እምብዛም አያገኙም ነበር፣ በዚህም የእንስሳትን መኖ ሳይቀር ለመመገብ መገደዳቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች አሉን” ብለዋል።

“የጅምላ ግድያ ስለመፈፀሙ የሚጠቁሙ እምነት የሚጣልባቸው ማስረጃዎች” አሉን ሲሉ ገልፀው፤ “ሰዎች ይህንን አሰቃቂ ሁኔታ ለመሸሽ ሲሞክሩ የጥይት እሩምታ ሳይቀር ይከፈትባቸዋል” ብለዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates