ዲፕሎማሲ

ሶማሌላንድ የሶማሊያን አዲስ ኢ-ቪዛ “ህገ-ወጥ” ነው አለች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/03/2018፡- የፕሬዚዳንት አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ ኢሮ መንግስት፣ አዲሱ የሶማሊያ ኤሌክትሮኒክ ቪዛ (ኢ-ቪዛ) በሶማሊላንድ ውስጥ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል።

እ.ኤ.አ ከሕዳር 10 ቀን 2025 ጀምሮ፣ የሶማሊያ ኢ-ቪዛ የያዙ መንገደኞች ወደ ሶማሌላንድ መግባት እንደሚከለከሉ የተዘገበ ሲሆን፤ ሃርጌሳ በድንበሯ ውስጥ ስርዓቱን “ህገ-ወጥና የሌለ” አድርጓ ትቆጥረዋለች ተብሏል፡፡

የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ወደ አየር ክልሏ የሚገቡም ሆነ የሚያቋርጡ በረራዎች አሁን ፍቃድ ማግኘት ያለባቸው ከሞቃዲሾ ሳይሆን ከሲቪል አቪዬሽን ሚኒስቴሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እርምጃው በሁለቱ መንግስታት መካከል በአየር ክልል ቁጥጥር፣ በሉዓላዊነትና በድንበር ዙሪያ ያሉ ውዝግቦችን እንደሚያባብሰው ተነግሯል፡፡

ወደ ሶማሌላንድ የሚበሩ ተጓዦች ከሶማሊያ ኢ-ቪዛ ይልቅ በሃርጌሳ ኢጋል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የቪዛ የመድረሻ ስርዓትን እንዲጠቀሙ ባለሥልጣናቱ መክረዋል፡፡

አየር መንገዶችም ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሳሆን ማንኛውም ወደ ሶማሌላንድ ለሚጓዙ መንገደኞች የሶማሊያን ኢ-ቪዛ ደንብ የሚያስፈጽም አየር መንገድ፣ የሶማሌላንድ የአየር ክልልን ሊያጣ ይችላል ተብሏል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates