ኢትዮጵያ
መነሻውን ከሱዳን ያደረገ የተበላለት የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ በአማራ ክልል ቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/02/2018፡- የጦር መሣሪያው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቅዋል።
የጦር መሳሪያው “ለህገ-ወጥ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ ነው” ተብሏል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ “ለህገ-ወጥ ቡድኑ ሊደርስ የነበረ፣ 1 ክላሽ ጠመንጃ፣ 10 የክላሸ ካዝና፣ 566 የዲሽቃ ጥይት፣ 8260 የብሬን ጥይት፣ 4779 የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር ውሏል” ብለዋል።
በ4 ሞተር ብስክሌት የተጫነ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ በቋራ ወረዳ ምርት ገለጎ ቀበሌ አድርጎ “ጠላት” ሲል ለጠራው አካል ሊደርስ የነበረ መሆኑን ገልጸዋል።



