አፍሪካ

“የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አስታራቂ መሆን አትችልም” ስትል ሱዳን አስታወቀች፡፡

በሌላ በኩል ጄነራል አል-ቡርሃን፡ የሱዳን ሕዝብ አይሸነፍም፣ ጠላትን ለመደምሰስና ሀገሪቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ቃል ኪዳን ኣለው ሲሉ ተደመጡ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/02/2018፡- የሱዳን የተኩስ አቁም ድርድር፤ ሱዳን ቱርክ እና ኳታር በአገሯ የተከሰተውን የእርስ በርስ ጦርነት ለመፍታት አስታራቂዎች መሆናቸውን አስታውቃለች

ሱዳን የአሜሪካን የሰላም ድርድር ጥሪ እንደምትቀበልም የገለፀች ስትሆን ሆኖም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን እንደ አስታራቂ እንደማትቀበል ይፋ አድርጋለች።

የኢንዶኔዥያ የሱዳን አምባሳደር ያሰር መሐመድ አሊ በጃካርታ ከአንታራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አገራቸው ለሰላም ድርድር ቅርብ እንደሆነች ነገር ግን በሽማግሌዎች ጉዳይ ላይ እንደማትስማማ ተናግረዋል።

ሳውዲ አረቢያ፣ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እንድያስታርቁ በአሜሪካ ተሰይመዋል ያሉት አምባሳደሩ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለሃምዳን ዳጋሎ ታጣቂዎች ግልጽ ድጋፍ በመስጠቷ በሱዳን መንግስት ተቀባይነት እንደሌላት ተናግረዋል።

አምባሳደር ያሰር መሐመድ አሊ ግብፅ እና ሳውዲ አረቢያ ከሱዳን መንግስት ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግሮ ቱርክ፣ ኳታር እና አረብ ኤምሬትስ ሽማግሌዎች ሊሆኑ እንደማይችሉ መግለፃቸው አንታራ ሚዲያ ዘግቧል።

ይህ እንዲህ እያለ ጄነራል አል-ቡርሃን፡ የሱዳን ሕዝብ አይሸነፍም፣ ጠላትን ለመደምሰስና ሀገሪቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ቃል ኪዳን ኣለው ሲሉ ተደመጡ፡፡

ትላንት፣ ከሱዳን ጦር ኃይሎች ተንቀሳቃሽ አመራር ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ የሉዓላዊነት ምክር ቤት ሊቀመንበር እና የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን፣ የጦር ሠራዊቱን ጽናት እና የሱዳን ሕዝብ በጠላትነት ፊት አንድነትን የሚያረጋግጥ ጠንካራ ንግግር አድርገዋል።

ለተሰዉት ወታደሮች ጸሎት በማቅረብ ንግራቸው የጀመሩት አልቡርሃን፣ “የሱዳን ሰማዕታት” ብለው በመጥራት እና እግዚአብሔር የቆሰሉትን እንዲፈውስ እና የጠፉትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያገናኝ ተማፅነዋል፡፡

ይህ ጦርነት የሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን የመላው አገሪቱ ጦር እንደሆነ አፅንዖት በመስጠት፣ አል-ቡርሃን የሱዳን ሕዝብ “በፍፁም እንደማይሸነፍ” እና “በዚህ ሕዝብ ስም የሚዋጋ ሁሉ እንደማይሰበር” ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ዜጎችን የጦር ኃይሉ “ጠላትን ለማጥፋት እና የሱዳንን መንግሥት እስከ ዳር ድንበሯ ድረስ ለማስጠበቅ” ተልዕኳቸውን ለመቀጠል ቆርጠው እንደተነሱ አረጋግጠዋል።

አል-ቡርሃን በግጭቱ ውስጥ የውጭ ተሳትፎን በግልፅ በመጥቀስ “ይህ ጥቃት፣ በጠበኝነት እና በእብሪት በተሞሉ አገሮች የተደገፈው በቅርቡ ይሰበራል” ሲሉ የሱዳን ሕዝብ እንደሚያሸንፍ አረጋግጠዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates