አፍሪካ
ፕሬዝደንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን ሃያ ሀገራት “መወገድ አለባት” ሲሉ ተናገሩ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/02/2018፡- የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሚያሚ ውስጥ ለአሜሪካ ቢዝነስ ፎረም በሰጡት ቃለ ምልልስ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን ሃያ ሀገራት አባልነቷ መነሳት አለባት ብለዋል።
በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በቀጣይ ከሕዳር 22 እስከ 23 በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ በሚካሄደው የቡድን ሃያ ሃገራት ጠቅላላ ጉባኤ እንደማይገኙም ፕሬዝደንት ትራምፕ ተናግረዋል።
ምክንያታቸውን ሲገልጹም፤ “ምክንያቱም በደቡብ አፍሪካ ያለው ነገር ጥሩ አይደለም፤ ደቡብ አፍሪካም ከዚህ በኋላ የቡድን ሃያ ሀገራት አባል ሆና መቀጠል የለባትም” ብለዋል።
በትራምፕ ፋንታ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝደንት ጀ.ዲ. ቫንስ በጉባኤው ለመገኜት እቅድ መያዛቸውንም ቲ.አር.ቲ አፍሪካ ዘግቧል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ “ደቡብ አፍሪካ ነጭ ገበሬዎችን ከመሬት ባለቤትነታቸው ተፈናቅላለለች፤ መሬታቸውንም ትወርሳለች፤ ሀገሪቱ በተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ እጅግ ዘግናኝ ጫና ታደርሳለች” በሚል ደቡብ አፍሪካን በተደጋጋሚ ሲወነጅሉ መቆየታቸውን ይታወሳል፡፡



