መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል የኤርትራን አገዛዝ ደጋፊ ነው ያለቸውን ግለ ሰው አባረረች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/02/2018፡- የእስራኤል ባለሥልጣናት የኤርትራ አገዛዝ ደጋፊ እንደሆነ የተነገረለት አንድ ኤርትራዊ ዜጋ ከሀገሪቱ ማባረራቸው ተዘገበ።

የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን እርምጃው በሀገሪቱ የኢሚግሬሽን አፈጻጸም ፖሊሲ በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ዘግበዋል።

ኤርትራዊው ግለሰብ እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም. በሕገወጥ መንገድ ወደ እስራኤል ገብቶ በሀገሪቱ ይኖር የነበረ ሲሆን ፖሊስ ትልቅ ስለት ከእጁ ላይ በማግኘቱ እና ቤተሰቡን በማስፈራራት ወንጀል ተጠርጥሮ በሚያዚያ 2025 በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

በእስር ላይ እያለ፣ ባለሥልጣናት የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ መሆኑን አረጋግጧል የሚሐው መረጃው፤ በዚህም ጉዳዩ ለእስራኤል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀርቦ፣ ሚኒስቴሩም በእስራኤል የኢሚግሬሽን ሕግ መሠረት ከሀገር እንዲወጣ አዟል።

በዚህ መሰረትም ትናንተናው ዕለት የሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን የግለሰቡን የማባረር ሂደት አከናውኗል።
ይህ እርምጃ በግልጽ የአገዛዝ ደጋፊ እንደሆነ የተለየ ኤርትራዊ ዜጋን እስራኤል ከሀገር ስታስወጣ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ተገልጿል።

ግለሰቡ ከእስራኤል ወደ አዲስ_አበባ እና ካምፓላ ከበረረ በኋላ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ መድረሱን ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እያለ 44 ኤርትራዊያን በኬንያ አንድ ቤት ውስጥ ተደብቀው መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ኤርትራዊያኑ በኡጋንዳ ድንበር አካባቢ በሚገኘው ቡንጎማ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ መገኘታቸው ፖሊስ አስረድቷል፡፡ ኤርትራዊያኑ በወታደራዊ ተሸከርካሪ ተጭነው በመምጣት እዚያ ቤት ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን የአይን እማኞች ተናግሯል፡፡
ከተያዙት 44 ኤርትራዊያን ውስጥ ህፃናት፣ ሴቶችና ወጣቶች የሚገኙበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ጣቢያ እንዲታሰሩ ታውቋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates