በሶማሊያ እና በሶማሊላንድ ውዝግብ በአየር ክልል ዙሪያ ውዝግብ እንደተፈጠረ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/02/2018፡- ሶማሊያ እና ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ባወጡት እርስ በእርሱ የሚጋጭ የበረራ ፈቃድ እና የቪዛ መመሪያ ምክንያት በሶማሊያ የአየር ክልል ውጥረት ነግሷል ተባለ።
ይህ ክስተት አየር መንገዶችን እና መንገደኞችን ግራ ያጋባ ሲሆን፣ በርካታ መንገደኞችን ከጉዟቸው አስተ ተብሏል።
የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አውሮፕላኖች ከሞቃዲሾ የኤሌክትሮኒክ ቪዛ ያልያዙ መንገደኞችን እንዳያሳፍሩ ያዘዘ ሲሆን፣ ይህንን ሕግ የተላለፈ የበረራ እገዳ ሊያጋጥመው እንደሚችል ማስጠንቀቁን ተዘግቧል።
የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን እና አየር ማረፊያዎች ሚኒስቴር በበኩሉ ያለ ፈቃድ ወደ ግዛቲቱ የአየር ክልል የሚገባ ማንኛውም አውሮፕላን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚጠብቀው የሚገልጽ ሌላ መመመሪያ አውጥቷል።
ሚኒስቴሩ ሁሉም የሰላማዊ መንገደኞች እና የንግድ በረራዎች ወደ ግዛቷ ከመግባታቸው በፊት ፈቃድ ማግኘት አለባቸው ብሏል።
ፈቃድ ያላገኘ ማንኛውም በረራ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት እንደጣሰ የሚቆጠር መሆኑን እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚጠብቀውም ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።
ይህ የበረራ መመሪያ ከሰባት ቀናት በኋላ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ መመሪያው ሶማሊላንድ ግዛቷን፣ የውሃ አካሏን እና የአየር ክልሏን እንድቆጣጠር ይፈቅድልኛል ያለችውን የቺካጎ ሲቪል አቪዬሽን ስምምነትን ያከበረ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።



