የትራምፕ አማካሪ፡ የሱዳን ጦር ለሰብአዊ ተኩስ አቁም መስማማቱ የአሜሪካው ፕሬዝዳነት አማካሪ ማሳድ ቦሎስ ገለፁ።
በስምምነቱ ዝርዝሮች ጉዳዮች ላይ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/02/2018፡- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ ልዩ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ የሱዳን ጦር ለሶስት ወራት የሚቆይ የሰብአዊነት ስምምነት ተነሳሽነትን በመርህ ደረጃ እንደማይቃወም ተናግረዋል።
ከሁለቱም ወገኖች የመጀመሪያ አቀባበል እንደተደረገላቸው እና የአሜሪካ ጥረቶች በአሁኑ ጊዜ የስምምነቱን ዝርዝሮች በማጠናቀቅ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ቡሎስ ጉዳዩ የክትትል እና የአፈፃፀም ዘዴዎችን ጨምሮ “ውስብስብ ቴክኒካዊ፣ የደህንነት እና የሎጂስቲክስ ዝርዝሮች” ስላሉት በእነዚህ እየተሰራ ነው ብሏል።
ግቡ ከጦርነቱ በኋላ ለሚደረገው ሂደት መንገድ የሚጠርግ አጠቃላይ ግንዛቤ ላይ መድረስ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል፣ ይህም በኳድ መግለጫ ላይ የተጠቀሰው የዘጠኝ ወር እቅድ አካል እንደሆነ በመግለፅ “ሁለቱም ወገኖች በመርህ ደረጃ ተስማምተዋል፣ እና ከሁለቱም ወገኖች ምንም አይነት የመጀመሪያ ተቃውሞ አልቀረበም። አሁን በጥሩ ዝርዝሮች ላይ እያተኮርን ነው።” ሲሉ ተደምጧል።
በሱዳን ውስጥ ያለውን የሰብአዊነት ሁኔታ “በጣም አጣዳፊ” ሲሉ የገለፁት ቦሎስ፣ በኤል ፋሸር የተከሰተው ነገር የተወገዘ” መሆኑን አክለዋል፣ ይህም ወደ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ሱዳናውያን እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ነው መድረሱን አክሏል።
የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ በኤልፋሻር እየፈፀመው በሚገኘው ግፍ እስካሁን ወደ 70 ሺ ሰዎች ሲፈናቀሉ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፁ ተገድሏል።



