ዲፕሎማሲ

ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በደቡብ ኮሪያ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት ሮኬቶች መተኮሷ ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/02/2018፡- ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ የመከላከያ ሚኒስትሮች ሁለቱን ኮሪያዎች የሚያዋስነውን አካባቢ እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ሮኬቶችን ተኮሰች።

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ሳምንት ከበርካታ የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓቷ ወደ 10 የሚጠጉ ሮኬቶችን መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል፡፡

ሮኬቶቹ በምዕራባዊ የፓስፊክ ውቅያኖስ በሚገኘው የውሃ ክፍል ላይ ሲሆን፥ ሮኬቶቹ ያደረሱት ጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝ የመከላከያ ሚኒስትሮቹ ተናግረዋል፡፡

ሮኬቶቹ የተወነጨፉት የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሰትና የደቡብ ኮሪያ አቻቸው አህን ጂዩ ባክ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ በሆነው አካባቢ ካደረጉት ጉብኝት አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በተመሳሳይ ከቀናት በፊት የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሊ ጄ ምያንግ ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር በተገናኙበት የእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ስብሰባ ወቅት የመድፍ ሮኬቶችን ተኩሳለች ሲል የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ከስሷል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates