የተለያዩ
በኬንያ ያጋጠመው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 26 ከፍ አደረገው፡፡
የጎርፍ አደጋ ደግሞ የህይወት አድን ጥረቱ ፈታኝ አደርጎታል ተብለዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/02/2018፡- በምዕራብ ኬንያ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ዛሬ አራት ተጨማሪ አስከሬኖች ከተገኙ በኋላ የሟቾች ቁጥር ወደ 26 ከፍ እንዳለ ተዘግበዋል፡፡
ይሁን እንጂ በድንገተኛ ጎርፍ ምክንያት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት መቆሙ ተገልፀዋል።
የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኪፕቹምባ ሙርኮመን እንዳሉት 25 ሰዎች አሁንም እንደጠፉ እና መንግስት የፍለጋ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥለዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ቅዳሜ ዕለት ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት አደጋ መንገዶች ሙሉ በሙሉ በመቆረጣቸው ወደ አካባቢው ለመድረስ ወታደሮች አራት አውሮፕላኖችን መጠቀማቸውን ተናግረዋል።
እሁድ ዕለት፣ በኬንያ ሪፍት ቫሊ ክልል ውስጥ በቼሶንጎች አካባቢ ከሚገኝ ኮረብታ ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ በኋላ የፍለጋ ቡድኖች ቦታውን ለቀው መውጣታቸው ተነግረዋል።
በኬንያ በዘነበው ከባድ ዝናብ በብዙ አውራጃዎች የጎርፍ መጥለቅለቅ እንዳጋጠመ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል።
መንግስት ለጎርፍ እና መሬት መንሸራተት በተጋለጡ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች እንዲንቀሳቀሱ አሳስቧል፡፡
መንግስት ከ30 በላይ የቆሰሉ ሰዎችን የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን እና ቤቶቻቸው በጎርፍ የተወሰዱባቸውን በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችን እንደሚደግፍ ተናግረዋል።



