አፍሪካ

አሜሪካ ሉዓላዊነቴን በሚያስከብር መልኩ የእስላማዊ አማፂያንን ለመከላከል ድጋፍ የምታደርግ ከሆነች ደስተኛ ነኝ ስትል ናይጀሪያ አስታወቀች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/02/2018፡- ናይጄሪያ የግዛቷ አንድነት እስከተከበረ ድረስ የአሜሪካን የእስላማዊ አማፂያንን ለመዋጋት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀበል ገልጻለች፡፡

ይህም በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን በደል በተመለከተ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለወታደራዊ እርምጃ ዛቻ ማሰማታቸው ተከትሎ ነው። ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ናይጀሪያ የክርስቲያኖችን ግድያ መግታት ካልቻለች የመከላከያ ሚኒስትሩ በናይጄሪያ ውስጥ “ፈጣን” ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ እንዲዘጋጁ ጠይቀዋል።

«ግዛታችንን እስካከበረች ድረስ የአሜሪካን እርዳታ በደስታ እንቀበላለን» ሲሉ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቢ አማካሪ የሆኑት ዳንኤል ብዋላ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ነገር ግን ትራምፕ እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የአሜሪካ ጦር ወደ ናይጄሪያ ወታደሮችን ማሰማራት ወይም እዚያ ያሉትን “እጅግ ብዙ” ክርስቲያኖችን መግደል ለማስቆም የአየር ድብደባ ሊፈጽም ይችላል ማለታቸውን ይታወሳል።

ትራምፕ ናይጄሪያን «የተዋረደች አገር» ብለው ቢጠሩዋትም ዳኒኤል ብዋላ ግን «ዶናልድ ትራምፕ ስለ ናይጄሪያ ጥሩ እንደሚያስቡ ስለምናውቅ ቃል በቃል አንወስደውም» ብለዋል።

ከ200 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እና ወደ 200 የሚጠጉ ጎሳዎች ያሏት ናይጄሪያ፣ በሰሜን በአብዛኛው ሙስሊሞች በደቡብ ደግሞ በአብዛኛው ክርስቲያን የሚኖሩባ ናት።

እንደ ቦኮ ሃራም ያሉ እስላማዊ አማፂያን ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ ከ15 ዓመታት በላይ ከፍተኛ ውድመት ፈጽመዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችንም ገድለዋል፣ ነገር ግን ጥቃቶቻቸው በአብዛኛው በአገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ብቻ የተወሰነ ነው፣ ይህም አብዛኛው ሙስሊም ነው።

 

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates