አፍሪካ
ድንበር የለሽ የዶክተሮች ቡድን በሱዳን አል ፋሸር ዓመፅ እየጨመረ በሄደበት ወቅት የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይሉ ሲቪሎች ከቀጠናው እንዲወጡ እንዲፈቅድ አሳሰበ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 24/02/2018፡- ድንበር የለሽ የዶክተሮች ቡድን በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ውስጥ ያለው ሁኔታ እና በነዋሪዎች ላይ የሚፈጸሙ በደሎች እየተባባሱ በመምጣታቸው በመጠቆም የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች እና ሌሎች ተባባሪ የታጠቁ ቡድኖች ሲቪሎች ከሱዳን አል ፋሸር ከተማ እንዲወጡ ወዲያውኑ እንዲፈቅዱ ጥሪ አቅርቧል።
“RSF እና ተባባሪ የታጠቁ ቡድኖች ሲቪሎችን እንዲያድኑ እና ከኤል ፋሸር እንዲሸሹ እንዲፈቅዱላቸው በአስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን” ሲሉ የቡድኑ የአደጋ ጊዜ ኃላፊ ሚሼል ኦሊቪየር ላቻራይት ተናግረዋል።
እንዲሁም የኳድ አባላት – አሜሪካ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ግብፅ – በከተማው ውስጥ ያለውን የደም መፍሰስ ለማስቆም ያላቸውን አቅም እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
ቡድኑ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን እና በአል ፋሸር ውስጥ የሰብአዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲሄድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ “ጥግ ይዞ መመልከት እንደማይችል” አስጠንቅቋል።
የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ኤልፋሻርን ከተቆጣጠረ ባኃላ በንፁሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ወንጀሎች ሲፈፀም የሚያሳዩ ምስሎች መውጣታቸው ይታወሳል፡፡



