ዲፕሎማሲ

ግብፅ የኤርትራን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር ድጋፍ አደርጋለሁ አለች።

የኤርትራዉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ከትላንት ጀምሮ በግብፅ የአምስት ቀናት ጉብኝት እዬደረጉ ነው።

ኢትዮሞኒተር፡21/02/2018፡- የግብፅ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አልሲሲ፤ የኤርትራን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲከበር ካይሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ታደርጋለች ሲሉ ቃል ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በካይሮ ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ለአምስት ቀን የሚቆይ ጉብኝት ለማድረግ ካይሮ መግባታቸው ይታወሳል።

በዚህም የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከኤርትራው አቻቸው ጋር በካይሮ በተወያዩበት ወቅት፤ ሀገራቸው ለኤርትራ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል።

“ግብፅ ከኤርትራ ጋር ባላት ሥር የሰደደ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ትኮራለች” ሲሉም አል ሲሲ በውይይታቸው ተናግረዋል።

“በተለያዩ መስኮች በተለይም በኢኮኖሚ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር” ያላቸውን ፍላጎትም አጽንኦት መስጠታቸውን አናዶሎ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ በበኩላቸው፤ “ግብፅ በአፍሪካ ቀንድና በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና መረጋጋትን በማጠናከር እና የልማት ጥረቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያው ትብብር  ጥልቅ ጠቀሜታ አለው” ሲሉ ተደምጠዋል።

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ይህ የግብፅ  የአምስት ቀን ጉብኝት እቅድ፤ ኢትዮጵያ የአሰብ የ’ይገባኛል’ ጥያቄ በተደጋጋሚ እያነሳች ባለችበት ወቅት ነው።

ባለፈው ማክሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያ ተዘግታ አትኖርም ማለታቸው ይታወሳል።

በአል ሲሲ እና በኢሳያስ መካከል የተካሄደው ዉይይት ቀጠናዊ ጉዳዮችን የዳሰሰ ሲሆን፤ በሱዳን እየተካሄደ ስላለው ጦርነትም ተመልክቷል።

ሁለቱም መሪዎች በሱዳን ባለው ጦርነት ላይ ያላቸው አቋም ተመሳሳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ብሔራዊ መንግሥታዊ ተቋማቱን ወይም የሱዳን ጦር ኃይሎችን ለመመደገፍ ቃል ገብተዋል።

በጀነራል ሃምዳን ደጋሎ ወይም ሂሜቲ የሚመራዉን የትይዩ መንግሥት እንደማይቀበሉት አረጋግጠዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates