አፍሪካ

በአል ፋሺር የሱዳን ህዝብን ሲገድል የነበረውን አቡ ሉሉ የተባለው የፈጣን ድጋፍ ሐይሎች አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተዘገበ።

ኢትዮሞኒተር፡21/02/2018፡- እየዞረ ንፁሃኑን ሲገድል የነበረውን ታጣቂ በራሱ በፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ተይዞ እንደታሰረ ተዘግቧል።

ፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ኤልፋሻርን ከተቆጣጠረ በኃላ በንፁሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፅሙ የሚያሳዩ ምስሎች በስፋት ሲዘዋወር ተስተውሏል።

ይህ በእንዲህ እያለ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት በሱዳን ኤል-ፋሸር ላይ የፈጣን የድጋፍ ኃይሎች ጥቃትን አውግዟል።

የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ሐሙስ ዕለት በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ኤል-ፋሸር ላይ የፈጣን የድጋፍ ኃይሎች (RSF) እየጨመረ በመጣው የኃይል እርምጃ “ከባድ ስጋት” እንዳላቸው አናዶሉ ዘግቧል።

የጸጥታ ምክር ቤቱ አባላት ባወጡት መግለጫ “ብድኑ በሲቪሉ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ግፍ፣ ግድያዎችን እና የዘፈቀደ እስራቶችን ጨምሮ እየፈፀመ ያለወን ግፍ አውግዘዋል።
ግፉም ዘርን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።

የፈጣን ድጋፍ ሐይሉ ጥቁር ወይም የዓረብ ዘር የሌላቸውን ዒላማ አድርጎ እየገደለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

የኤል-ፋሸርን ከበባ እንዲያነሳ እና ውጊያው በአስቸኳይ እንዲቆም የሚጠይቀውን ውሳኔ 2736 (2024) በማስታወስ፣ አባላቱ አርኤስኤፍ የዚህን ውሳኔ ድንጋጌዎች ተግባራዊ እንዲያደርግ “በጥብቅ” አሳስበዋል።

አባላቱ ሁሉም የጥሰቶች ፈጻሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በሱዳን ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ከዓለም አቀፍ ሕግ ጋር በሚስማማ መንገድ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ያልተገደበ የሰብአዊ ተደራሽነት እንዲፈቅዱ እና እንዲያመቻቹ ጥሪ አቅርበዋል።

“ሲቪሎችን ለመጠበቅ እና ከተማዋን ለቀው ለመውጣት ለሚሞክሩ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል” ሲል መግለጫው አመልክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates