ፖለቲካ

የአፍሪካ ህብረት ለስምንተኛ ጊዜ የካሜሩን ፕሬዝደንት ሆነው ለተመረጡት ፖል ቢያ የደስታ መልዕክት ማስተላለፉን አነጋጋሪ ሆኗል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/02/2018፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሐመድ አሊ ዩሱፍ እ.አ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2025 በካሜሩን በተካሄደው ምርጫ ለስምንተኛ ጊዜ ለተመረጡትና ሀገሪቱን ለ43 ዓመታት ለመሩት አዛውንቱ ፕሬዝደንት ” በማሸነፍዎ ደስ ብሎኛል ” ሲሉ የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ፕሬዝደንቱ በማሸነፋቸው ደስታቸውን ይግለጹ እንጂ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰው ሁከት፣ የተቃዋሚዎችና ከምርጫው ውጤት ጋር ግንኙነት ያላቸው የፖለቲካ ተዋንያን እስርና አፈና ግን እጅጉን አሳስቦኛል ብለዋል።

በካሜሩን ሰላም እንዲሰፍንና ወደ መረጋጋቷ እንድትመለስ ሁሉም የፖለቲካ ተዋንያን ተቋማዊ በሆነ መልኩ አወንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዩሱፍ፣ ፖል ቢያ ምርጫውን ቢያሸንፉም ሁሉን አካታች የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የ92 ዓመቱ አዛውንት ፖል ቢያ፣ በተያዘው የጥቅምት ወር እንዳሸነፉ የተነገረለትን የስልጣን ዘመን ሲጨርሱ አንድ መቶኛ ዓመታቸውን ይደፍናሉ። ይህም ዕድሜያቸውን እኩሌታም በፕሬዝደትነት አሳልፈዋል እንደማለት ነው።

መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ግን የደስታ መልዕክቱን አስተላልፏል። በዚህም ስልጣን የሙጢኝ ለሚሉ የአፍሪካ መሪዎች የመበረታታት ያክል ነው በማለት በዙዎች እየተቹት ይገኛሉ።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates