አፍሪካ
ኢጋድ በኤልፋሸር የተከሰተውን ሁከት አወገዘ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/02/2018፡- የኢጋድ ሥራ አስፈፃሚ በኤል ፋሸር የተከሰተውን ሁከት አውግዞ በሱዳን የሚገኙ ሲቪሎችን ለመጠበቅ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ከተማዋን እንደተቆጣጠሩ ከተዘገበ በኋላ በሰሜን ዳርፉር በኤል ፋሸር ከፍተኛ የሰብአዊ ጥሰት ተግባራት እየተባባሰ በመምጣቱ ከፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉንም የዓመፅ ድርጊቶች አጥብቀው ያወገዙ ሲሆኑ ግጭቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በሱዳን የሲቪሎች ስቃይ መቆም እንዳለበት እና ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን የማክበር፣ ህይወትን የመጠበቅ እና ያልተገደበ የሰብአዊነት እርዳታ የመፍቀድ የሞራል እና የህግ ግዴታ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
ዋና ፀሐፊው በሱዳን ውስጥ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰብአዊ ጥረቶችን በፍጥነት እንዲደግፉ እና ውይይትን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።
“ኢጋድ ጦርነቱን ለማስቆም እና የሲቪሎችን ጥበቃ ለማረጋገጥ ሁሉንም እውነተኛ ጥረቶች ለመደገፍ ዝግጁ ነው” ሲሉም አረጋግጠዋል።



