የተለያዩ

ከ36 ሺሕ በላይ የቪዛ ጊዜያቸውን ያሳለፉ የውጭ ሀገር ዜጎች መቀጣታቸው ተገለጸ፡፡

ኢትዮ ሞኒር፡ 13/02/2018፡- በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺሕ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር መመለሳቸውን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ እየተሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በዘርፉ በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ሀገራዊ አቅም መጠናከሩን አመልክተዋል፡፡

ለአብነትም በአዲስ አበባ በተካሄዱ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎች የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ያለምንም እንከን መስተናገዳቸውን ጠቅሰዋል።

በቪዛ አገልግሎት ወደ 188 ሀገራት የመዳረሻ (ኦን አራይቫል ቪዛ) ተጠቃሚዎች ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህም የ24 ሰዓት የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት ያለው መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የተለያዩ የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውን እና በዚህም በሕገ ወጥ ሰንሰለት የተሰማሩ 26 ሰዎች ተጠያቂ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺሕ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲመለሱ መደረጉን መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት 4 ሚሊየን ፓስፖርት ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉንም ወ/ሮ ሰላማዊት አስታውቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates