ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ አለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡12/02/2018፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “ህገ ወጥ ስራዎችን” ያከናውናሉ ባላቸው የሃዋላ አስተላላፊዎች ላይ “የማያዳግም” “ሰፊ እርምጃ” ለመውሰድ መዘጋጀቱን የባንኩ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ።

ባንኩ የሚወስደው እርምጃ “የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ህግን የጠበቀ” እንደሚሆን የገለጹት የብሔራዊ ባንክ ገዢው፤ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና “አስፈላጊውን ጥንቃቄ” እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ዶ/ር እዮብ “የመጨረሻ” ያሉትን ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት፤ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ የሃዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው። የብሔራዊ ባንክ ገዢው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያቀኑት፤ የዓለም ባንክ ግሩፕ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ዓመታዊ ስብሰባዎችን ለመካፈል ነው።

የብሔራዊ ባንክ ትኩረት “በርካታ የገንዘብ አስተላላፊ ተቋማት ህጋዊ በሆነ መንገድ ሰርተው ዘላቂነት ያለው ቢዝነስ ውስጥ እንዲቆዩ ነው” ያሉት ዶ/ር እዮብ፤ ሆኖም የተወሰኑ ድርጅቶች “የአጭር ጊዜ ትርፍ” ለማግኘት “በህገ ወጥ ስራ” ላይ ከመሰማራት እንዳልተቆጠቡ አስረድተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates