ከሱዳን ኤል ፋሸር ከበባ ለማምለጥ ወደ 350 የሚጠጉ ቤተሰቦች 50 ኪሎ ሜትር ተጉዘዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡12/02/2018፡- ትናንት ጥቅምት 11 ወደ 350 የሚጠጉ አባወራዎች የተከበበውን የሱዳን ከተማ ኤል ፋሸርን ሸሽተው ለአራት ቀናት 50 ኪሎ ሜትር ያህል በእግራቸው ተጉዘው በታዊላ ከተማ በአስከፊ ሁኔታ መድረሳቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች ማክሰኞ አስታውቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው አብዛኛዎቹ ሴቶች፣ ህጻናት እና አዛውንቶች በመንገድ ላይ የተጎዱ ከሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኤል ፋሸር እና አካባቢው የተፈናቀሉ ከ600,000 በላይ ሰዎች አሁን በታዊላ ይገኛሉ።
ከቡድኑ ጋር አብረው የሸሹ በደርዘን የሚቆጠሩ ወጣቶች አሁንም እንደጠፉ እና በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ያለውን ግፍ እየከፋ መምጣቱን ድርጅቱ ገልፀዋል፡፡
“የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የሰብአዊ አጋሮቹ ለአዲሶቹ ስደተኞች የምግብ፣ የውሃ እና መሰረታዊ የህክምና አገልግሎት ቢያቀርቡም ከሚያስፈልጉት ግብዓቶች እጅግ የላቀ ነው” ብሏል ጽህፈት ቤቱ። “ብዙ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች መጠለያ፣ በቂ ምግብ ወይም ንፁህ ውሃ የላቸውም። OCHA ከባለስልጣናት፣ ከለጋሾች እና አጋሮች ጋር ተጨማሪ አቅም፣ ግብዓቶችን እና ድጋፍን በማሰባሰብ እየሰራ መሆኑም አስታውቀዋል።”
በኤል ፋሸር ተደጋጋሚ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎቹ ተናግረዋል። በኤል ፋሸር በጣም ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን አደጋ ላይ መውደቁን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
OCHA የአካባቢው ባለስልጣናት እንደዘገቡት በግዛቱ ዋና ከተማ በ127 ቦታዎች ከ109,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን፣ አብዛኛዎቹ በምግብ፣ የንፁህ ውሃ እና የህክምና አገልግሎት እጦት ወድቀዋል።